2015 Adama Science and Technology University Application Procedure | Check ASTU Full Application Procedure.

Adama Science and Technology University Application Procedure 2015 | Check ASTU Full Application Procedure.

Adama Science and Technology University Application Procedure 2015… Adama Science and Technology University, ASTU first and second Application Procedure for the 2015 academic session are out. See more details below;

Adama Science and Technology University Admission Letter

Are you aware that the Adama Science and Technology University has officially released her highly Application Procedure 2015, provisional Application Procedure, which contains the names of all Programs, successfully Released for the 2015 academic session.

Contents

ASTU Application Procedure 2015

How to Access the ASTU Provisional  Application Procedure 2015

Who can apply to the New ASTU?

ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2010 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠልና የአገሪቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በስሩ የተደራጁትን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማዕከላት በማድረግ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን እያፈራ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በ2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ 2009 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱና ከታች የተጠቀሱትን ዝርዝር መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በቀጥታ (online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋል፡፡
የመመዝገቢያ መስፈርቶች:-

  • በኢንጂነሪንግ ትምህርት መስክ መሰልጠን ለሚፈልጉ:- ለታዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ), ለወንዶች ከ410 በላይ፣ ለሴቶች ከ400 በላይ የሆነ, ለሌሎች ክልሎች:-
    ለወንዶች ከ425 በላይ፣ ለሴቶች ከ410 በላይ የሆነ
  • በአፕላይድ ሳይንስ ትምህርት መስክ መሰልጠን ለሚፈልጉ:– ለታዳጊ ክልሎች:-ለወንዶች ከ350 በላይ፣ ለሴቶች ከ335 በላይ የሆነ- ለሌሎች ክልሎች:-ለወንዶች ከ375 በላይ፣ ለሴቶች ከ350 በላይ የሆነ
    የትምህርት መስኮች:-
READ ALSO:  University of Malawi Mature Entry Requirements Intake for The 2022/2021 Academic Year
  አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ   አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
 ኢንጂነሪንግ  አፕላይድ ሳይንስ  ኢንጂነሪንግ  አፕላይድ ሳይንስ
አርክቴክቸር ባዮቴክኖሎጂ አርክቴክቸር አፕላይድ ባዮሎጂ
ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ ሲቪል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ኬሚስትሪ
ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን ኬሚካል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ፊዚክስ
ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ጅኦሎጂ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ጅኦሎጂ
ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ኤሌክትሮኒክስ ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ማቲማቲክስ
ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ
ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ
ማይኒንግ ኢንጂነሪንግ ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ

የምዝገባ ጊዜ:- ከነሐሴ 15 እስከ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ምዝገባው የሚጠናቀቀው:- ነሐሴ 21 ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ይሆናል::
የምዝገባ ቦታ:- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ cba.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ::
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን:- ጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓ.ም.  ከጧቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11:30 ሰዓት
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ:- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል::

READ ALSO:  2015 PESC Information Systems College Admission Requirement | Check PESC Full Admission Requirement.

ማሳሰቢያ:-
1)    ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣
2)    ከሚመዘገቡት አመልካቾች ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው በድህረ-ገፅ:-
www.most.gov.et    www.aastu.edu.et      www.astu.edu.et
እንደአመቺነቱም በስልክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚገለፅ ይሆናል::
3)    አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም የመሰናዶ (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል::
4)    ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል::
5)    አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2009 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል::
6)    የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም::
7)    በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል::
8)    በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል::
9)    በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ መፈተኛ ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው::
10)    በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው::

READ ALSO:  2022/2021 Catholic University of Malawi Route 2 Admission Through Bridging Programme

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ የተጠቀሱትን ድህረ ገፆች መጎብኘት ይቻላል::               የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

Leave a Reply