Bahir Dar University Seminar for Amharic Language Development Institute (STI) 2018 Schedule

0
SHARE

Bahir Dar University Seminar for Amharic Language Development Institute (STI) 2018 Schedule, the sixth English language and cultural seminars

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም (አቋማተ) ስድስተኛው የአማርኛ ቋንቋና የባህል ዘርፎች አገር አቀፍ አውደ ጥናት በዋናው ግቢ አዳራሽ ከሚያዝያ 16-17/2010 ዓ/ም ድረስ ያካሂዳል።

በአውደ ጥናቱ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም (አቋማተ) ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር መለሰ ገላነህ ሲሆኑ እንደርሳቸው ገለጻ አማርኛ የግዕዝን የውል ቋንቋነት ውርስ በኢትዮጵያ ማገልገል ከጀመረ በርካታ ሽህ ዘመናት እንዳስቆጠረና ቋንቋው ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የቤተ መንግስት የስራ ቋንቋ ሆኖ በማገልገል ላይ የሚገኝ እንደሆነና በዘመናዊት ኢትዮጵያ ብሄራዊ ወይም የስራ ቋንቋ ሆኖ ማገልገል ከጀመረ 160 አመታት በላይ እንዳስቆጠረ፣ አማርኛ በሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች የጋራ መግባቢያ ሆኖ በማገልገል ላይ እንደሆነ፣ በበርካታ የተግባቦት አመቶች እያገለገለ ያለ ቋንቋ መሆኑና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማገልገል ከጀመረም ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ እንዳስቆጠረና ከኢትዮጵያ አልፎ በአሜሪካ ሀገር በሚገኙ ግዛቶችና በእስራኤል እና በአንዳንድ አረብ ሀገራት የመግባቢያ ቋንቋ እንደሆነ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። አማርኛ በውጭ ሀገራት እንደኮርስም ሆነ እንደ ትምህርት ቋንቋነት እያገለገለ እንደሚገኝና አማርኛን በኮርስ ደረጃ በጣሊያን ሀገር ለመስጠት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  ሂዩማኒቲስ ፋካሊቲ ጋር ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ገልጸው ነገር ግን ይህ ሁሉ የአማርኛ አብርክቶት /እሴት/ ቢኖርም ግን አሁንም የአማርኛ ቋንቋ ልማት በሚጠበቀው መልኩ እየተከናወነ አለመሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ ጠቁመዋል። በቋንቋው ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ በብቸኝነት እየሰራ ያለው ተቋም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም (አቋማተ) እንደሆነና ተቋሙ በቋንቋው ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት የተለያዩ የማህበረሰብና የምርምር ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የአውደ ጥናት ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

የአማርኛ ቋንቋ በሴማዊ የቋንቋ ግንድ ከሚመደቡ የአለም ቋንቋዎች በተናጋሪ ብዛት ሁለተኛ እንደሆነና የእድሜ ባለጸጋነቱንና የብዙ ተናጋሪ ባለቤትነቱን ያህል እንደሌሎች ቋንቋዎች በልጽጎ በየዘመኑ ልክ የሚያስፈልገውን ሁሉ ማድረግ የሚያስችል ቁመና አለው ወይ የሚለውን አስቸጋሪ ጥያቄ ለመመለስ ከባድ እንደሆነና የቀድሞ አባቶቻችን የራሳችን የሆነ ቋንቋና ፊደላትን አስረክበው ቢያልፉም ለተከታታይ ትውልዶች የማበልጸግ ስራ ባለመስራታችን ኢትዮጵያዊ የሆኑ ቋንቋዎችን በተለይም አማርኛ በውድቀት ላይ እንደሆነ የቅርብ ጥናቶች እንደሚያመለክቱ የተናገሩት በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ብዙአየሁ ቀሪሰው ናቸው። አክለውም ቋንቋው ከመግባቢያነቱ አልፎ የተጠቃሚውን ሁለንተናዊ አውድ የተሸከመ ከመሆኑ አንጻር ውድቀቱ የማንነት ውድቀት እንደሚሆንና የቋንቋ የእድገት ደረጃ የተጠቃሚውን የአስተሳሰብ ልዕልና፣ የማስታወስ ችሎታ፣ ችግርን የመፍታትና የፈጠራ የክህሎት ደረጃ እንደሚወስንና እነዚህ ጉዳዮች ከግለሰብ አልፈው የማህበረሰብና የሀገርን የእድገት ደረጃ ወሳኝ በመሆናቸው የቋንቋችንን የውድቀት ምክንያቶችን መርምረን መፍትሄ በማፈላለግ የማበልጸግ ስራ በርትተን ካልሰራን የሚታሰበው የሀገር ዕድገት ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ይህን ችግር በመገንዘብ የቋንቋውን እድገት ችግሮችን ለማጥናትና የአማርኛን ቋንቋ የማበልጸግና የሚበለጽግበትን መንገድ ቀይሶ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሆነ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የሁሉም አይነት እውቀት መጠቅለያ፣ ማውጫና ማውረጃ እንደ እንግሊዝኛ ያለ ሀያልና ዘመናዊ ቋንቋ እንደሌለና ለአለም ሁሉ በሚባል ደረጃ በሽያጭም ሆነ በእውቀትና መረጃ የሚቀርበው በዚህ ቋንቋ እንደሆነና ኢትዮጵያዊያንም የምንጨልፈው በዚሁ ቋንቋ በመሆኑ የገበያው ተሳታፊና አትራፊ ለመሆን ከዚህ የተሻለ እድል መፍጠር እንደሚያስፈልግና ምክንያቱም ህዝባችን እንግሊዝኛን ጠንቅቆ አለማወቅና ተጠቃሚ አለሆን እንደሚታይብንና ለዚህም ገበያተኛ ለመሆን ያለአማራጭ እንግሊዝኛን በወጉ ማወቅና በሱ መጠቀም ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የራሳችንን ቋንቋዎች ማበልጸግና የቴክኖሎጂው መቀባበያ ማድረግ እንደሚያስፈልግና እንግሊዝኛውን በወጉ አውቆ በወጉ መጠቀም ግን በአሁኑ አያያዝ አስቸጋሪ በመሆኑና ከደርግ ዘመን ጀምሮ የቋንቋም ሆነ አጠቃላይ የትምህርት ስነ-ዘዴና ስርዓተ ቋንቋውን በደንብ አውቆ ሌላውንም ለማወቅ እንዳላስቻለና እጀ ሰባራ እንዳደረገን የገለጹት በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ቁልፍ ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር ባየ ይማም ናቸው። ፕሮፌሰሩ አክለውም ሀሳብ ሳይንስን ቋንቋ አፍኖን ብዙ ጉዳት እንዳደረሰብንና ከሳሪ እንጂ አትራፊ አለመሆናችን ገልጸው ነገር ግን አማራጩ እንግሊዝኛን ማስተማሪያ ሳይሆን አንብቦ መረጃ ማድረጊያ መሆን እንዳለበትና በድህረ ገጽ ይሁን በፊት ለፊት የማስተማሪያ ዘዴ የራሳችንን ቋንቋ መጠቀምና ማበልጸግ አስፈላጊ እንደሆነና በራሳችን ቋንቋ ማሰብ፣ ያሰብነውን መተግበር የምንችለው የእኛውን ቋንቋ መጠቀም ስንችል እንደሆነ ገልጸዋል።

CONNECT WITH US: Like our Facebook Page,Follow Us On Twitter, AND also Subscribe to Our Feed. Stayed Blessed!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here